እንኳን ወደ አማራ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ድረ-ገጽ በሰላም መጡ


ከሀምሌ 01/2009ዓ.ም እስከ ታህሳስ 06/2010ዓ.ም ድረስ 3,874,304,930.53 (36.90%) ብር ገቢ መሰብሰቡን ባለስልጣኑ አስታወቀ።

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን በ2009 በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢ ብር 9,190,000,000 እና የከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 1,310,000,000 በድምሩ 10,500,000,000 ለመሰብሰብ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ከሀምሌ 01/2009 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የክልል ገቢ ብር 3,492,251,551.43 አፈጻጸም (38.00 %) እና የከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 382,053,379.10 አፈጻጸም (29.16%) በድምሩ ብር 3,874,304,930.53 አፈጻጸም 36.90%) የተሰበሰበ መሆኑን እየገለጽን የክንውን ሪፖርት 03 ገጽ አባሪ የላክን መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ...


የባህር ደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ለ137 ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠረ

በባህር ዳር ከተማና አካባቢዋ ስራ አጥ የነበሩ ወጣቶች የጫት ቀረጥና የአገልግሎት ክፍያ መሰብሰብ የሚያስችላቸውን ስምምነት ህዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም ከባህር ደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ጋር ለሁለት ዓመት የሚቆይ የውል ስምምነት ተፈራረሙ። የውል ስምምነቱ ዓላማ መንግስት በተለይም የከተማ አስተዳደሩን ገቢ በብዙ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንዲሰበሰብ በማስቻል ከገቢ አሰባሰብ ልዩ ባህሪ አንጻር የከተማውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት፣ ተጨማሪ ያንብቡ...


በአገልግሎት አሰጣጥ የህዝብ እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

የባለስልጣን ሰራተኞች በመልካም አስተዳደር፣ ውጤት ተኮር ስርዓት፣ የውጤት ተኮር ስርዓት የትግበራ ደረጃዎች፣ የዜጎች ቻርተር ፅንሠ-ሀሳብና አተገባበር፣ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ፣የመንግስት ሰራተኞች የስነ-ምግባር መመሪያ፣ እና የስብሰባ አፈጻጸም መመሪያ አስመልክቶ ከጥቅምት 22 እስከ 29 ቀን 2010 ዓ.ም የወስዱትን ስልጠና ስልጠና፣ የ2009 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2010 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ተጠናቀቀ። የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክተው የስራ መመሪያ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሀመድ አብዱ የስልጠናው መሰጠት የባለስልጣኑን ተልዕኮ ለማሳካት አጋዥ በመሆኑ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በየዕለቱ ካደረጋችሁት ውይይት መረዳት ችያለሁ። ተጨማሪ ያንብቡ...


ለአራተኛ ጊዜ ከሚያዝያ 23 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የነባርና አዲስ ግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ጥናት በአንድ ሳምንት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።

እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ከቅድመ-ዝግጅት እስከ ተግባር ምዕራፍ ያለውን የጥናት አፈጻጸም የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ ሲገመግም ጥናቱ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ተገንዝቧል። ነገር ግን የክልሉን ቀጣይ 5 ዓመታት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሚወስን በመሆኑ በሁሉም ዞንና ከተሞች እስካሁን ያለው ሁኔታ እንዲገመገም ወስኗል። እንዲሁም በጥናቱ ለሚያልፉ ነጋዴዎች ተከታታይ ትምህርትና ስለጠና መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል። በዞን ከተሞችና ወረዳዎች ያለው ወቅታዊ አፈጻጸም በተለያዩ መድረኮች ከግንቦት 03 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ለአንድ ቀን ይገመገማል ተብሎ ይጠበቃል። በክልሉ ሊጠና ከታቀደው ነባርና አዲስ 310,520 ነጋዴዎች መካከል እስከ ግንቦት 01 ቀን 2009 ዓ.ም 60,821 ወይም 19 .5 በመቶ መጠናቱን ተጠንቷል። በባህር ዳር ከተማ የቀን ገቢ ጥናት የሚያካሂዱ ሁሉም የኮሚቴ አባላት የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ ክብረት መሀመድ በተገኙበት ግንቦት 03/2009 ዓ.ም ሲገመግሙ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች ጥናቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ላደረጉትና ለሚያሳዩት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም በከተማዋ ፍትሃዊ የግብር አስተዳደር ስርዓት እንዲሰፍን የነዋሪው ህዝብ ደጋፍ እንዳይለየን በማለት መልእክት አስተላልፈዋል። ሌሎች ዞንና ከተሞችም ዛሬና ነገ ገምግመው መደበኛ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ታውቋል።


የግብር ከፋዮችን የቀን ገቢ ግምት ጥናት ለሚያካሂዱ የኮሚቴ አባላት የሚሰጠው ስልጠና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ክልል አቀፍ የአሰልጣኞች ስልጠናን ተከትሎ በዞን፣ ከተማ እና ወረዳ ቀበሌ ድረስ ቤት ለቤት እየተንቀሳቀሱ ስራውን ለሚያከናውኑ የጥናት፣ የኢንስፔክሽንና መረጃ አሰባሳቢ ባለሙያዎቸ የሚሰጠው ስልጠና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ከሚደርሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ባህር ዳር ከተማ ሚያዝያ 20 እና 21/2009 ዓ.ም በሚካሄደው የስልጠና የመክፈቻ ንግግርና የስራ መመሪያ የሰጡት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ምትኩ በላይ ናቸው። የግብር ከፋዮች ደረጃ ፍትሃዊ አይደለም፣ የግብር ስርዓታችሁ ትክክል አይደለም እያለ ጥያቄ የሚያነሳው ራሱ ግብር ከፋዩ ነው። ስለዚህ በዚህ መንገድ ትልቅ አደራና ትልቅ ሃላፊነት ስለተሰጣችሁ በታማኝነትና በቁርጠኝነት ወደ ስራ እንድትገቡ አደራ እላለሁ።... ተጨማሪ ያንብቡ...


ሚያዝያ 23/ 2009 ዓ.ም ለሚጀመረው የግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምት ጥናት ዞንና ከተሞች ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን እየገለጹ ነው።

ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደው የግብር ሥርዓት ማሻሻያ ኮሚቴ አመራሮች የውይይት መድረክ ከተሳተፉ አመራሮች መካከል የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ማለደ ጋር በቅድመ ዝግጅትና አንዳንድ ጉዳዮች ያደረግነው ቃለ -ምልልስ ይህንን ይመስላል::
አቶ ዘውዱ፤ በዞናችን በዚህ ዓመት የሚደረገውን የቀን ገቢ እና የደረጃ “ሐ” ቁርጥ ጥናት ግብር ለማካሄድ የራሳችንን ቅድመ-ዝግጅት አድርገናል። በ25ቱም ወረዳዎች ዞኑን ጨምሮ የህዝብ ግንኙነት እቅድና መመሪያዎችን በዓግባቡ የማደራጀት እና በተጨባጭ ከ26 ሺህ ያላነሱ ግብር ከፋዮች መረጃ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል።... ተጨማሪ ያንብቡ...


አማካይ የቀን ገቢ ጥናት ፍትሃዊ እንዲሆን የክልል፣ የዞን፣ የከተማና የወረዳ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ።

በአማራ ክልል ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደውን የግብር ከፋዮች ደረጃ ልየታ አማካይ የቀን ገቢ ጥናት ለማካሄድ በተያዘው ዕቅድ በምዕራብ በአማራ ከሚገኙ የግብር ሥርዓት ማሻሻያ ኮሚቴ አመራሮች ጋር በተካሄደ ውይይት የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ መንግስት ገቢ ይፈልጋል ይህንን በመረዳት በፈቃደኝነት፣ በሰሩት ልክ ለአገር አስተዋፅኦ ማበርከት አለብኝ እንዲሁም ግብር መክፈል ግዴታየ ነው ብለው ማንም ሳይቆጣጠራቸው የሚከፍሉ በርካታ ናቸው። በሌላ በኩል ትንሽ የማይባሉ ነጋዴዎች ደግሞ ግብር የመክፈል ሁኔታ አነስተኛ ነው። ግብር ላለመክፈላቸው በምክንያትነት የሚያነሱት ደግሞ የፍትሃዊነት... ተጨማሪ ያንብቡ...


ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የቁርጥ ግብር ጥናት እና የግብር ከፋዮች ደረጃ ልየታ ጥናት ከሚያዝያ 23 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ ታወቀ

የአማራ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በክልሉ የሚገኙ ግብር ከፋዮችን የቀን ገቢ በማጥናት ደረጃቸውን እንደገና እንደሚለይ የባለስለጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሀመድ አብዱ ሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት የቁርጥ ግብር ጥናት እና የግብር ከፋዮች ደረጃ ልየታ ጥናት ማካሄድ ያስፈለገው የገቢ ግብር አዋጅ 240/2008 ዓ.ም ተግባራዊ ለማድረግ፣ በክልላችን የደረጃ "ሐ” መደበኛ ቁርጥ ግብር ጥናት ከተጠና 5 ዓመቱን ያጠናቀቀ በመሆኑ በህጉ መሠረት በአዲስ ለማጥናት እና በታክስ አስተዳደር ስርዓቱ የግብር ከፋዮችን የህግ ተገዠነት ለማሻሻል ታስቦ ነው ብለዋል። ተጨማሪ ያንብቡ...

Next

Quick Contact
Useful Downloads
External Links

Copyright © 2017 Amhara Revenues Authority,AmRA. All Rights Reserved.

Site Visitors:
Last Update:22/04/2017