እንኳን ወደ አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ድረ-ገጽ በሰላም መጡ


የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ምስጉን ግብር ከፋዮችን ሸለመ።

በአዊ ብሔራብ ዞን አስተዳደር የ2011 በጀት ዓመት ዕቅደ አፈጻጸም እና በ2012 ዓ.ም የደረጃ ”ሐ” ግብር አሰባሰብ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማትና ግለሰቦች ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ አዊ ባህላዊ አዳራሽ ሽልማት ተሰጥቷል። በዕለቱ የተከበሩ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን የብሔረሰብ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ አጀበ ስንሻው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሃላፊ፣ ክብርት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አቡኔ ዓለም፣ አቶ አግማስ ጫኔ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር፣ አቶ ብርሃኑ አያሌው የገቢዎች መምሪያ ሃላፊ እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። ተጨማሪ ያንብቡ...


የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ3.2 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ዋና ተልዕኮ ለክልሉ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ግብዓት የሚውል የታክስ ገቢ በመሰብሰብ ለክልሉ መንግስት ማቅረብ በመሆኑ በ2012 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 14.1 ቢሊየን ብር በሌላም በኩል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 3,932,270,476 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 3,233.222,118.93 ብር ወይም 82.22 በመቶ ሰብስቧል። አፈጻጸሙ በ2011 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ብር 2665627228.45 ጋር ሲነጻጸር የ21.29 በመቶ ብልጫ ያሳየ ሲሆን በዚህ አፈጻጸም ዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞን አስ/ር ገቢዎች መምሪያ የተሻሉ ነበሩ በተቃራኒው ምዕራብ ጎንደር፣ ጎንደር ከተማ እና ደሴ ከታማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ዝቅተኛ አፈጻጸም የነበራቸው መሆኑን የቢሮው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል የስራ ሂደት ሃላፊ ገለፀዋል።


በ2012 በጀት ዓመት በደረጃ "ሐ" ግብር አከፋፈል የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የገቢ ተቋማት ሽልማት ተበረከተላቸው።

የደረጃ “ሐ” ግብር አሰባሰብ አስመልክቶ ግብር ከፋዮች ለቅጣትና ወለድ እንዳይዳረጉ በማሰብ በንቅናቄ ስራ ከሀምሌ 11 እስከ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም መቶ በመቶ በንቅናቄ ያስከፈሉ የአንደኛ ደረጃ እና የሜትሮፖሊታን ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀላቸውን የባጀጅ ሽልማት ከገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ብዙአየሁ ቢያዝን እጅ ቁልፍ ተረክበዋል። ተጨማሪ ያንብቡ...


የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ከመንግስት ልማት ድርጅቶች መካከል 76 ሚሊየን ብር በመክፈል የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ።

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አለማየሁ የሚከተለው መልዕክት አላቸው። ግብር ለመክፈል ግለሰብ ሆነ ድርጅት ትኩረት መስጠት አለባቸው፣ ትኩረት መስጠት ካልተቻለ እዛው የሚቀሩ ገንዘቦች ይኖሩና ኪሳራ ያሰከትላል። ለምሳሌ የተለያዩ ኪራዮች፣ ”ማሽን” ኪራዮች በአግባቡ ካልተሰበሰቡ ወደ መንግስት ሳይገቡ የሚቀርበት ሁኔታ ስለሚኖር ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።


በ2011 በጀት ዓመት የላቀ ሚና የነበራቸው ግለሰቦችና አጋር አካላት ተሸለሙ

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2012 ዓ.ም የደረጃ”ሐ” ግብር አሰባሰብ የላቀ ሚና ለነበራቸው ግለሰቦችና አካላት የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልል ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ ክቡር አቶ መላኩ አለበል በምክትል ርዕሠ-መስተዳድር መዐረግ የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ፣ የክልሉ፣ የዞን፣ የከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለተሻለ ገቢ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት፣ ሌሎች ዕውቅና የሚሰጣቸው ግብር ከፋዮች፣ አጋር አካላት፣ የገቢ ተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዝ እንግዶች በተገኙበት ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የሽልማትና የእውቅና... ተጨማሪ ያንብቡ...

Next

Quick Contact
Useful Downloads
External Links

Copyright © 2017-2020 Amhara Region Revenues Bureau. All Rights Reserved.

Last Update:03/02/2020