በ2011 በጀት ዓመት የላቀ ሚና የነበራቸው ግለሰቦችና አካላት ተሸለሙ።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2012 ዓ.ም የደረጃ”ሐ” ግብር አሰባሰብ የላቀ ሚና ለነበራቸው ግለሰቦችና አካላት የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልል ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ ክቡር አቶ መላኩ አለበል በምክትል ርዕሠ-መስተዳድር መዐረግ የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ፣ የክልሉ፣ የዞን፣ የከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለተሻለ ገቢ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት፣ ሌሎች ዕውቅና የሚሰጣቸው ግብር ከፋዮች፣ አጋር አካላት፣ የገቢ ተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዝ እንግዶች በተገኙበት ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የሽልማትና የእውቅና ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል።
የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ብዙአየሁ ቢያዝን እንደገለጹት የእለቱ መድረክ ዓላማ የክልላችንን ሁለንተናዊ ልማት ለመደገፍ ቁልፍ መሳሪያ ከሆኑት ተግባራት ውስጥ አንዱ ፍትሃዊ የግብር አስተዳደር ስርዓት ማስፈን፣ የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ በምናደርገው ጉዞ ላይ የላቀ አስተዋጸኦ ያበረከቱትን ለማመስገን እና ቀጣይ ላስቀመጥነው ትልቅ ግብ መሳካት የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ እና በ2012 በጀት ዓመት ሊሰበሰብ የታቀደው 14.1 ቢሊየን ብር ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ሃላፉነት እንዲወጣ ለማድረግ ነው ብለዋል።

በሌላም በኩል በ2011 በጀት ዓመት ግዴታየን እወጣለሁ መብቴን እጠይቃለሁ በሚል መሪ ቃል ህዝቡ የንቅናቄው አካልና ባለቤት እንዲሆን በማድረግ የተሰራው ስራ በበጀት ዓመቱ እንዲሰበሰብ ከታቀደው 12 ቢሊየን ብር 11.2 ቢሊየን ወይም 93.2 በመቶ እንድንፈፅምና ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅተ ጋር ሲነጻጸረ የ1.2 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዲያሳይ አድርጎታል።

በክልሉ ከ380 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ያሉ ቢሆንም ዛሬ ለዕውቅና የበቁት ከ37 ሺህ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መካከል እርስ በርስ በማወዳደር ስለሆነ በቀጣይ ሁሉም ለጋራ ልማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በየደረጃው የምስጋናና እውቅና ስርዓት እንደሚዘጋጅ በዚህ አጋጣሚ መግለፅ እወዳለሁ ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የአማራ ክልል ርዕሠ-መስተዳደር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው እንደገለፁት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በ2011 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና በ2012 የደረጃ ‘ሐ” አሰባሰብ ውጤት በተሰጠው የሽልማትና እውቅና አሰጣጥ ምክንያት በማድረግ ዛሬ ለሽልማት የበቃችሁ ግለሰቦችና አካላት እንኳን ደስ ያላችሁ እያልኩ ዛሬ የተሸለሙት ብቻ ሳትይሆ ሁሉም ግብር ከፋይ፣ ሁሉም ግብር ሰብሳቢ፣ ሁሉም ግብር በመሰብሰብ የተሳተፈ ባለድርሻ አካል ተሸላሚ ስለሆናቸሁ በክልሉ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤትና እና በራሴ ስም ማመስገን እወዳለሁ ብለዋል። ግብር መክፈል የስልጡን ማህበረሰብ አንዱ መገለጫ ነው። ግብር መክፈል የእውቀት፣ የሀብትና የብልዕግና ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግስት ግብር ካልሰበሰበ ለህብረተሰቡ የሚያሰፈልጉ ፍጆታዎችን ማሟላት አይችልም። የተለያዩ የመሠረተ-ልማት እና ሰላምን በክልላችን ለሟሟላት ግብር መሰብሰብ አስፈላጊ ነው።
ስለዚህ ግብር ለመክፈል ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻል እንዳለ ሁኖ ግብር በመሰብሰብ በኩል በተለይም በክልላችን አጠቃላይ የግብር አሰባሰብ ስርዓታችንን ስንፈትሽ መስፈርቱም መመዘኛው እጅግ በጣም ቀላል ነው። ክልሉ ከአጠቃላይ ወጪው ከክልል በግብር የሚሰበሰበው ገንዘብ ምን ያህሉን ይሸፍናል የሚለውን ብቻ ማሰብ ነው።

ስለዚህ ክልላችን በግብር መሰብሰብ ወደ ኋላ ከሚታዩት አካባቢዎች አንዱ ስለሆነ በክልላችን ውስጥ ያለው ማህበረሰብ ራሱን እንደ ስለጡን አድርጎ የሚመለከትና እውነትም የተሻለ ስልጡን እና የተማረ ማህበረሰብ ያለበት ክልል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ለፍትህና ነጻነት ራሱን የማይሰጥ ለሚያምንበት ነገር ሕይወቱን የሚከፍል ህብረተሰብ ያለበርት ስለሆነ ታማኝነት የኛ መገለጫና እሴት በመሆኑ ግብር መክፈል ከሁሉም በላይ ትንሿ ታማኝነት ስለሆነች ትንሿን ታማኝነት እንዳንሸረሽርና እንድንጠቀምባት አደራ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል።
ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ግብር ሰብሳቢው ቢሮ ቢሆን በተለያዩ ጊዜያት የግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱን ዐቅም ለማጎልበት የክልሉ መንግስት የወሰዳቸው ቁርጠኝነቶች አሉ እነሱን ተጠቅሞ ግብርን አሟጦ መሰብሰብ የስፈልጋል። ከነጋዴው ብቻ ሳይሆን ከኛም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዳሉ እነገነዘባለን። አንዳንድ ጊዜ ግብሮችን በወቅቱ ባለመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ይህንን ያህል አለብህ ብሎ ባለመናገር ከተጠራቀመ በኋላ ይህንን ያህል ስላለብሀ ክፈል ካልሆነ ደግሞ ይችን ያህል ብትከፍል ይህን ያህል ልቀንስልህ እችላለሁ ብሎ የሚደራደር ባለሙያ አሁንም ጉያችን ውስጥ አለ።
በሌላ በኩል ግብር ሰብሳቢው አካል ግብር ሰብሳቢ ሰራተኛውንና አጠቃላይ ማህበረሰቡን እንደጠላት በማየት ወደነሱ ሲሄድ በፍቅር የመቀበል ሳይሆን በጥላቻ የመመልከት አስተሳሰቦች አሉ። እነዚህን በዚህ ዓመት በምናደርጋቸው ስራዎች ሁለቱን የማቀራረብ፣ ችግር ያለበትን ደግሞ በህግና ብስርዓት ርምጃ የመውሰድ ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን።
ግብራችንን ለማስፋት አዳዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ግብር መረቡ እንዲገቡ እንሰራለን፣ ሌላ ቦታ ያሉ ግብር ከፋዮችም በተቻለ መጠን እዚህ እየሰሩ ያሉ ግብር ከፋዮችም ግብር ከፋይነታቸውን ወደ ክልሉ አድርገው የክልሉን ገቢ እንዲያሳድጉ እንደሚያበረታቱ ገልጸው
የያዝነው በጀት ዓመት ግብር ከፋዮችን ሳናሸሽ ተቀራርበን የምንሰራበት ይሆናል ብየ አምናለሁ። ስለዚህ ሁላችሁም ተጠናክራችሁ ባለፈው ዓመት ለተመዘገበው ውጤት እጅግ እያመሰገንኩ በዚህ በጀት ዓመትም የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ተጠናክረን ሳንቀያየም በፍቅር ብዙ ገቢ እንሰበስባለን የሚል ተስፋ አለኝ ለዚህም የክልሉ መንግስት ድጋፍና ክትትል እንደማይለይ ላረጋግጥ እወዳለሁ ብለዋል።

ጥቅምት 2012ዓ.ምQuick Contact
Useful Downloads
External Links

Copyright © 2017-2020 Amhara Region Revenues Bureau. All Rights Reserved.

Last Update:03/02/2020